ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚሳዔል ሙከራ እያደረገች ነው

ሰሜን ኮሪያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሚሳዔል ሙከራ እያደረገች ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ምንም እንኳ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዓለም እያስጨነቀ ቢገኝም ሰሜን ኮሪያን ግን የሚሳኤል ሙከራ ከማድረግ አላገዳትም።

ትናንት እሁድ ሰሜን ኮሪያ ሁለት የአጭር-ርቀት ሙከራ ለማድረግ ሁለት ሚሳኤሎችን ለሙከራ መተኮሷን የደቡብ ኮሪያ መንግሥት አስታውቋል።

የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ይህን የሰሜን ኮሪያ መንግሥት የሚሳኤል ሙከራን አጥብቆ ኮንኗል።

“የዓለም አገራት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጠበው እያለ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ተግባር ተቀባይነት የሌላው እና በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል” ብሏል የደቡብ ኮሪያ መንግሥት።

ይህ የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ጥሪ ከተሰማ በኋላ የሰሜን ኮሪያ መንግሥት የሙከራውን ስኬት ጠቅሶ የእራሱን ተግባር አወድሶታል።

የሰሜን ኮሪያ መንግሥት እስካሁን በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ስለመኖሩ ሪፖርት አላደረገም።

ይሁን እንጂ ባለሙያዎች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ይኖራሉ ብለው ይገምታሉ።

LEAVE A REPLY