ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለተጨማሪ 23 የሥራ ቀናት ዝግ ሆነው ይቆያሉ ተባለ።
ፍርድ ቤቶቹ ዝግ የሚሆኑት ከአርብ መጋቢት 25 ቀን 2012 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለተጨማሪ 23 የስራ ቀናት መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌስቡክ ገጸ ላይ ይፋ አድርጓል።
በዚህ ጊዜ ዳኞች ለውሳኔ የደረሱ እና ውዝፍ መዛግብት ላይ ውሳኔዎችን እየሰጡ እንደሚቆዩ፣ አስቸኳይ ጉዳዮችን በተለይም ከሰዎች መብት መከበር ጋር የተገናኙ፣ የሀገር ሰላምን እና ደህንነትን የተመለከቱ እና ወረርሽኙን በሚመለከት ሕጎች መከበራቸው አስፈላጊ ስለሚሆን እነዚህንን እና መሰል ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች እንደሚታዩም ገልጿል።
ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ጊዜያት ውስጥ በወንጀል ጉዳዮች ላይ በሚሰጥ ፍርድ ምክንያት ከእስር መፈታት ያለባቸው ካሉ በሚመለከተው ችሎት በሚሰጥ ትዕዛዝ የሚፈፀም እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡