ጠ/ሚ አብይ ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት ገደቡን ማሙላት አሉ

ጠ/ሚ አብይ ኢትዮጵያ በመጪው ክረምት ገደቡን ማሙላት አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ በመጪው የክረምት ወራት የሕዳሴ ግድብን የውሃ ሙሌት እንደምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ህዝቡ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን እንዲከላከልና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለመጨረስ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግድቡ ግንባታ የጀመረበትን ዘጠነኛ ዓመት በማስመልከት ባስተላለፉት በዚህ መልዕክት ሁለት ጉልህ ፈተናዎች ገጥመውናል ብለዋል።

እነሱም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝና የሕዳሴ ግድብ ግንባታን የተመለከተ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ “ሕይወታችንን ሊነጥቅ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የእያንዳንዳችን በር እያንኳኳ ከደጃችን ቆሟል” በማለት በሽታው የደቀነውን ስጋት ገልጸዋል።

ጨምረውም የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 26 ቢሆንም በሚቀጥሉት ሳምንታት ሊያሻቅብና ምናልባትም ሞት ሊያጋጥም እንደሚችል ጠቅሰው ወረርሽኙ ከተሞች አልፎ ወደ ገጠር መንደሮች እንዳይገባ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም የወረርሽኙ መከሠት በግድቡ ግንባታ ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ቢጠቅሱም በመጪው ክረምት የውሃ ሙሌት እንደሚጀመር ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY