ኮቪድ 19 የጋረጠብን አደጋ… || ሙሼ ሰሙ

ኮቪድ 19 የጋረጠብን አደጋ… || ሙሼ ሰሙ

ኮቪድ 19 የጋረጠብን አደጋ የቱንም ያህል አስከፊ እየሆነ ቢመጣ፣ አ/አ በሽተኛን ከመዘገብ፣ የሳኒቴሪ አቃ ከማቅረብና ተጠንቀቁ ከሚል ተማጽኖ የዘለቀ አማራጭ መፍትሔ የሌላት መሆኗን ከትናንቱ የም/ከንቲባው ንግግር ተረድቻለሁ።

ንግግራቸውን ከችግሩ ውስብስብነትና ፈታኝነት አኳያ ከመዘንነው የመፍትሔ አማራጮችን አርቆ የተመለከተ አልነበረም። የኮቪድ 19 አደጋን ከአንድ አቅጣጫ ያውም “የቤትና የምግብ አቅርቦት” የሌላቸውን ዜጎች ለመታገድ ከማሰብ መንገድ ብቻ መመልከት አስጊ ነው?! ቀሪዎቹ በሚሊዮን የሚቆጠሩና በተለያየ የኑሮ ደረጃ ያሉ ዜጎችስ ጉዳይ?! የክልሎችን ወሳኔ ማጤን ያሻል?!

አዲስ አበባ ለሁሉም የሚተርፍ አቅም እያላት ለ20 ቀን፣ የቀን ሰራተኛ ወገኖቿን በድጋፍ ከማቆየትና ጥሪታቸውን ሳያሟጥጡ እራሳቸውን እንዲያግዙ ከማድረግ ይልቅ ሞትን እንዲጋፈጡ አድርጋለች የሚል ስጋት አለኝ።

ከቀን ስራ ጋር በተገናኘ 70 በመቶ ያህሉ ስራ ቆሟል ለማለት ያስደፍራል። ለቀን ሰራተኛ የሚሆኑ የምግብ አቅርቦቶች ተቋርጠዋል፣ ምግብ ቤቶች ተዘግተዋል። ጥቃቅን የጉልበትና የአገልግሎት ስራ ማሰራት ቅንጦት ወይም ስጋት እየሆነ ነው። እንግዲህ የተከበሩ የም/ከንቲባው ውሳኔ በዚህ ትርምስ ውስጥ የሚላስ የሚቀመስ የሌለው የቀን ሰራተኛ በየቀኑ ከምግብ ፍላጎቱ በላይ ከፍተኛ ወጭ እያወጣ ጭምበል አጥልቆ፣ ሳኒታይዘር ተጠቅሞና ርቀቱን ጠብቆ “የሞተ” ስራ ሰርቶ እራሱን ከበሽታው እየታደገ ህይወቱን ያቆያል የሚል የተዛባ ድምዳሜ ላይ የተመሰረተ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

የበሽታው ስርጭት ፈጣን ስለሆነ “የውድቀት ደረጃ” ላይ ለመድረስ ጥቂት ሳምንታት ይበቃዋል። ያኔ ማህበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ቀውሱ በአስገዳጅ ሁኔታ መቀስቀሱና ስራ ሙሉ ለሙሉ መቋረጡ አይቀርም። ከተማችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ በሽተኞችን ይዛ፣ ለጋሽና ቀባሪ በሌለበት ሁኔታ መፍትሔው ምን ሊሆን ይችላል? አሁንም፣ እድላቸውን ይሞክሩ ይሆን !?

በተቃራኒው ግን አ/አን ለተወሰነ ቀን ዘግቶ የበሽታውን ዑደት በመግታትና ስርጭቱን በመቆጣጠር በሚሊዮኖች የመቆጠሩ ዜጎችን ከእልቂት መታደግ ይቻላል። የአንድ ወገን ሙግት ብቻ በመያዝ በሽታው በአስገዳጅ ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወንጀል “መብት” እስኪሆን ድረስ እንጠብቅ ማለት ግን ምን አይነት መፍትሔ እንደሆነ ለመረዳት የሚያዳግት ነው¡¡¡

ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ ቀወስን በመፈተሽ አማራጭ መፍትሔ ለማግኘት ከምሁራን ጋር መመካከር ግዴታ ነው። ከሕገ መንግስትስ አኳያ ይህንን አይነት ሀገር አቀፍ አደጋ ሲጋረጥብን ውሳኔ የመስጠት ስልጣን የስራ አስፈጻሚው ነው? ወይስ የምክር ቤቶቹ !? ወይይት ይጋብዛል!?!!

LEAVE A REPLY