መጋቢት 2012
አዲሱን የብርሃኑ ነጋን ንግግር ሰማሁት፤ ልዩ ነበረ፤ ሳይንገዳገድ በስሜት ያደረገው ትክክለኛና እውነተኛ፣ ያየውንና የሰማውን ፍርጥርጥ አድርጎ ተናገረው፤
ብርሃኑ ነጋን የማየው እንደታናሽ ወንድሜ ነው፤ ያስታወቀንና ያዛመደን የወያኔ እስር ቤት ነው፤ ስለዚህም ለሱ ያለኝን ስሜት መደበቅ አልችልም፤
የብርሃኑ ትልቁ ድካሙ ሰውን ቶሎ ማመኑ ነው፤ ልቡ ሰፊና ደግ ነው፤ ጥቃትን በጣም ይጠላል፤ ማንም ሲጠቃ አይቶ በይሉኝታ አያልፍም፤ ይህንን በተደጋጋሚ አይቻለሁ፤ እመሰክራለሁ፤
ብርሃኑ አብረው ከሚሠሩት ጋር ሁሉ ሙሉ እኩልነትን የሚያሳይ ነው፤
ብርሃኑ ሌላም ከኢትዮጵያ ፖሊቲካ ዋና ፈተና ነጻ ነው፤ ዕድሜ ለአባቱና ለእናቱ፣ እሱም በራሱ ያካበተው የሚበቃውን አካብቷልና በምቾት መኖር የሚያስችል ሀብት አለው፤
የዛሬው ንግግር ዋና ድክመት ያለው ስለምርጫው ታማኝነት በተናገረው ላይ ነው፤ ኃላፊነቱን በሙሉ ሥልጣን በሌለው የምርጫ ቦርድ ላይ የጣለው ይመስላል፤ ብዙ መሠረት የሌላቸው ‹‹ይገባኛሎች›› ተደርድረዋል፤
የብርሃኑ ነጋ ንግግር የፖሊቲከኛ ሳይሆን የትልቅ ብቁ ምሁር ንግግር ነው፤
አንድ ሌላ የብርሃኑ ለውጥ የሰማሁት የእናቱ መንፈስ ተንፍሶበት ‹‹ፈጣሪ አገራችንን ይባርክ!›› ማለቱ ነው፤
ብርሃኑ ነጋ ያቀረበው ንግግር ለዓቢይ አህመድ አንቅልፍ የሚያሳጣ ነው፤ ብርሃኑን ማዳመጡ በጣም ይጠቅመዋል፡፡