ፈረንሣይ ለጋሲዮን ካለ ክሊኒክ ያመለጠ የኮረና ቫይረስ ተጠርጣሪ በሰፈሩ ወጣቶች ተያዘ

ፈረንሣይ ለጋሲዮን ካለ ክሊኒክ ያመለጠ የኮረና ቫይረስ ተጠርጣሪ በሰፈሩ ወጣቶች ተያዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ አምስት ሰዐት አካባቢ የኮሮና ቫይረስ ሊኖሮበት እንደሚችል የተጠረጠረ አንድ ጎልማሳ ለሕክምና ከሄደበት ክሊኒክ በሩጫ ቢያመልጥም ብዙም ሳይርቅ በአካባቢው ወጣቶች ሊያዝ ችሏል::

በተለምዶ  ፈረንሣይ ለጋሲዮን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ  “ሐና ማርያም ክሊኒክ” ውስጥ ራሱን ቼክ አፕ ለማድረግ የመጣው ጎልማሳ ለክሊኒኩ ሠራተኞች የሳልና የራስ ምታት ስሜት እንዳለው በመግለፅ ነገሩን ቀለል አድርጎ ለመመልከት ያደረገው ጥረት እና ሁኔታው ያጠራጠራቸው የሕክምና ባለሙያዎች ባደረጉለት ሠፊ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች እንደሚታይበት በማረጋገጣቸው ለተሻለ ምርመራ ወደ ለይቶ ማቆያ መወሰድ እንዳለበት እንደነገሩት የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን  ገልጾልናል።

ሲታይ በጥሩ ጤንነት ላይ ያለ የሚመስለው እና ብቻውን ወደ ክሊኒኩ የመጣው ግለሰብ ግን የሕክምና ባለሙያዎቹን ምክር ካለመስማቱ ባሻገር በተቋሙ ውስጥ ሌላ ታካሚና አስታማሚ አለመኖራቸውን በመልካም አጋጣሚነት በመጠቀም ሮጦ ቢያመልጥም ተከትለው ወጥተው የጮኹትን ነርሶችና የፅዳት ሠራተኞች ድምፅ የሰሙ የአካባቢው ወጣቶች በሩጫ ደርሰውበት ሊይዙት ችለዋል።

በሁኔታው እና ግለሰቡ በፈጸመው ብዙዎችን ለእልቂት ለሚዳርግ ተግባር የተበሳጩ በርካታ ነዋሪዎችን አረጋግተው ወደ ፖሊስ ጣቢያና ለኮሮና ጥቆማ ወደ ተቋቋመው አካል ስልክ በመደወል በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በፀጥታ ኃይሎች ታጅቦ ለመጣው ህጋዊ አካል ተጠርጣሪውን ማስረከባቸውን መረጃውን በስፍራው ተገኝቶ ካጣራው የኢትዮጵያ ነገ ዘጋቢ መረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY