ኢትዮጵያ በኮረና ቫይረስ ሶስተኛ ሰው መሞቱን አሳወቀች

ኢትዮጵያ በኮረና ቫይረስ ሶስተኛ ሰው መሞቱን አሳወቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አሁን በማህበራዊ ሚዲያ ይፋ ባደረጉት መሰረት ሦስተኛዋ ታማሚ በዛሬው እለት ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።

የ65 ዓመት የዱከም ከተማ ነዋሪ ሴት የሆኑት ታማሚ በተጓዳኝ በሽታ ታመው የነበሩ ሲሆን የኮሮና ሕመም ምልክት ከታየባቸው በኋላ ነበር ወደ ለይቶ ማከሚያ የገቡት ሲል የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታውቋል።

በሁኔታው የተሰማቸውን ከፍተኛ ሀዘን የገለጹት የጤና ሚኒስትሯ ታማሚዋ በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 28 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገቡበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ዶ/ር ሊያ በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ በማለት በፌስ ቡክ ገጻቸው የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY