ከዱባይና ቱርክ የመጡ 2 ኢትዮጵያውያን ሴቶች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ከዱባይና ቱርክ የመጡ 2 ኢትዮጵያውያን ሴቶች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ሁለት አዳዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መገኘታቸው ዛሬ ይፋ ተደርጓል:: ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ286 ሠዎች በተደረገ ምርመራ ነው ሁለቱ አዲስ የከቪድ 19 ተጠቂዎች የተገኙት።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ  ዶክተር ሊያ እንደ ገለፁት ከሆነ ሁለቱም በቫይረሱ የተያዙት ሠዎች ኢትዮጵያውያን ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመው ግለሰቦቹ ቀደም ሲል ወደ ሀገር ቤት የገቡና የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።

የ24 ዓመት ወጣት የሆነችው አንደኛዋ ሴት ወደ ለይቶ ማቆያ የሚያስገባው አስገዳጅ ህግ ከመውጣቱ በፊት ከዱባይ የመጣች ሲሆን የ35 ዓመቷ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ደግሞ ከቱርክ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣች በኋላ በለይቶ ማቆያ ሆና ክትትል ሲደረግላት ቆይቶ ቫይረሱ የተገኘባት መሆኑ ታውቋል።

በዚህ መሠረት አሁን በኢትዮጵያ የሚገኙት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 71 የደረሰ ሲሆን 10 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውና ሦስት ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY