ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ የባህል ሕክምና ማኅበር ለኮሮና ቫይረስ ሕክምና ይሆናሉ ብዬ ያዘጋጀኋቸው መድኃኒቶች ቢኖሩም የትኛውም የመንግሥት አካል ሊመረምርልኝ ፍቃደኛ አልሆነም ሲል አስታወቀ።
እኛ በዛ ያሉ የባህል ሐኪሞችንና ለቫይረሱ የሚሆኑ የተለያዮ መድኃኒቶችን ብናዘጋጅም መንግሥት ስለ አንድ ግለሰብ ብቻ ትኩረት በመስጠት ሌላውን መርሳቱ ተገቢ አይደለም በማለት ከእውቋ የባሕል ሐኪም ወ/ሮ አበበች ጋር በኮሮና ቫይረስ መድኃኒት ዙሪያ እየተሠራ ያለውን እንቅስቃሴ ማኅበሩ ኮንኗል።
ለማንኛውም ሀገር በቀል እውቀት በሩ ክፍት መሆኑን ለሸገር ራዲዮ የገለጸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በበኩሉ እስካሁን እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ለተቋሙ አለመቅረቡን ጠቅሰው ከውጭ ሀገራት ተሞክሮ አንፃር ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
የአዲስ አበባ የባሕል ሕክምና ማኅበር ፕሬዝዳንት መሪጌታ መንግሥቱ ኦለታ ለኮሮና ቫይረስ ሕክምና ይሆናሉ፣ በሳይንሳዊ መንገድም ቢመረመሩ ለውጥ ያመጣሉ ብለው የተለያዮ አባሎቻቸው ያመኑባቸው መድኃኒቶች ቢዘጋጁም መንግሥት ተቀብሎ ለመርመር ፍላጎት አልባ ከመሆኑ ባሻገር ትኩረቱን አንድ ሰው (ሐኪም አበበች) ላይ ብቻ ማድረጉ እንዳሳዘናቸው ይፋ አድርገዋ