ቢል ጌት ፋውንዴሽን ለኮሮና የሚውል 200 ሚሊየን ብር ለአዲስ አበባ መስተዳደር ሰጠ

ቢል ጌት ፋውንዴሽን ለኮሮና የሚውል 200 ሚሊየን ብር ለአዲስ አበባ መስተዳደር ሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዓለም ዐቀፉ ባለሀብት ግብረ ሰናይ ድርጅት የሆነው “ቢል ጌት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ” የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳ  200 ሚሊዮን ብር እርዳታ ለአዲስ አበባ መስተዳደር  ሰጠ።

ድርጅቱ አሳሳቢውን የኮቪድ 19 ቫይረስን ለመቆጣጠር የገንዘብ ድጋፉን ያስረከበ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አረጋግጠዋል።

በተያያዘ ዜና ግዙፉ ቶታል ኢትዮጵያ የ17 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።  አንድ መቶ ሺኅ ሳኒታይዘር፣ ለአምቡላንሶችና ለኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት መኪኖች የአንድ ሚሊዮን ብር ነፃ የነዳጅ መሙያ ካርዶች እንዲሁም የእጅ ንፅህና መጠበቂያ መሣሪያዎችን አበርክቷል።

ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ካምፓኒ (ኮካ ኮላ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለሚደረገው እንቅስቃሴ የሚውል አምስት ሚሊዮን ብር ለግሷል።  ኩባንያው 3 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፉን ለቀይ መስቀል ሲያበረክት ቀሪውን የሳኒታይዘርና የምግብ ድጋፍ ለአዲስ አበባ እንዲሁም የኩባንያው ፋብሪካዎች ለሚገኙበት ባህር ዳር እና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደሮች መስጠቱን ከደረሰን ዜና መረዳት ችለናል።

LEAVE A REPLY