ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዐረቢያ ሀገራቸው እንዲመለሱ እየተደረጉ ያለው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አለመሆኑን መንግሥት አስታወቀ።
ሁለቱ ሀገራት ባላቸው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሠረት ቀደም ሲልም ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ እንደነበር ያስታወሰው መንግሥት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 2 ሺኅ የሚጠጉ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን አረጋግጧል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሆነው ከተመዘገቡት ሰዎች መሀል አብዛኞቹ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በዱባይ በኩል የሚመጡ መሆናቸው ከዐረብ ሀገራት የሚለሱት ሰዎች በዜጎች ዘንድ የስጋት ምንጭ መሆናቸው ሲገልጽ ሰነባብቷል።
ሳዑዲ ዐረቢያ ህገ ወጥ ናቸው ያለቻቸውን ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እያደረገች ቢሆንም ሀገራቱ በመረጃ ልውውጥ መሠረት ኢትዮጵያ ለተመላሾቹ የለይቶ ማቆያ ቦታዎችን ማዘጋጀቷን ስታረጋግጥ ተመላሽ ስደቸኞቹ እንዲሳፈሩ የሚደረግ መሆኑም ተነግሯል። ሳዑዲና ዱባይን ጨምሮ ከመካከለኛው ምስራቅ የሚመጡት ስደተኞች ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።