በቅናሽ ዋጋ የሚሸጡ የፊት ጭምብል የሚያመርት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

በቅናሽ ዋጋ የሚሸጡ የፊት ጭምብል የሚያመርት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኅብረተሰቡ በቅናሽ ሊያገኛቸው የሚችል የፊት መሸፈኛ ማስኮችን ለሚያመርቱ ሥራ ፈጣሪ ዲዛይነሮች እገዛ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

“ሶሻል ኢንተርፕራይዝ  ኢትዮጵያ” የተሰኘ ማኅበር “ዋዝ ኪድስ ኢትዮጵያ” በማለት  የሰየመውን ዘመቻ አስጀምሯል።  ዘመቻው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ኅብረተሰቡ በአካባቢው ባሉ ነገሮች በመጠቀም ኪስን በማይጎዳ የፊት መሸፈኛ በማዘጋጀት እንዲጠቀም የሚያስችል ነው ተብሏል።

በማህበራቱ የተሰናዳውና “ሽፋን ኢትዮጵያ” በሚል የተሰየመው ይህ ዘመቻ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የማስክ ተጠቃሚን ፍላጎት በመጨመር የሥራ ፈጠራ ላይ የተሠማሩ ወጣት የፋሽን ዲዛይነሮች አንድ ሚሊዮን ማስኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ ቸሚያበረታታ መሆኑም ተነግሮለታል።

LEAVE A REPLY