ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተጠቃች የምትገኘው ኢትዮጵያ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የተላኩ የቻይና የህክምና ባለሙያዎችን አዲስ አበባ ገቡ።
የኮቪድ 19 ቫይረስ መነሻና ክፉኛ ተጠቂ የሆነችው ቻይና አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ በሽታውን መቆጣጠር በመቻሏ የክፉ ቀን ባለውለታዋ የሆነችው ኢትዮጵያ ሀገራችንን ለመታደግ እንቅስቃሴ ጀምራለች::
ዐሥራ ሁለት አባላትን የያዘው የያዘው የቻይና የህክምና ባለሙያዎች ቡድን በዛሬው እለት ነው አዲስ አበባ የገባው።
የህክምና ባለሙያዎቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ታውቋል።