ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሕዝብ ከቤት እንዳይወጣ የተለያዮ ስልቶችን እየተጠቀመ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የቤት አውቶምቢሎችን እንቅስቃሴ የሚገድብ አሠራር ይፋ አድርጓል።
መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የቤት ተሽከርካሪዎች ከዛሬ (ኮድ-2) በፈረቃ ሊንቀሳቀሱ የሚያስገድድ አሠራር መዘርጋቱን ገልጿል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም በሚኒስትሮች ኮሚቴ የወጣ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም እና አተገባበር ዙሪያ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 የሆኑ የቤት ተሽከርካሪዎች በሰሌዳ ቁጥራቸው ሙሉና ጎዶሎነት በፈረቃ እንደሚንቀሳቀሱ ግድ ነው ተብሏል።
በወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት የሰሌዳቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ ወይም ዜሮ የሆኑ ሽከርካሪዎች ዛሬ ዓርብ የሚንቀሳቀሱ፤ የሰሌዳ ቁጥራቸው መጨረሻ ጎዶሎ የሆነ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ነገ ቅዳሜ ይንቀሳቀሳሉ ተብሏል።ፈረቃው ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣዮቹ አምስት ወራት ተግባራዊ ይሆናል፡፡ መመሪያውን ክልሎችም እንደራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አሠራር ዘርግተው እንዲተገብሩትም ታዟል።