ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ አራት አዳዲስ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መሆኑን ተከትሎ በአገሪቱ በኮቪድ 19 ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ዘጠና ስድስት ደርሷል::
የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስ ቡክ ገፃቸው ጉዳዮን አስመልክተው ባሰፈሩት መረጃ ባለፉት 24 ሰዐታት የላብራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 842 ሰዎች መካከል አራት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል በለዋል።
ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ የታወቀው ሁሉም ሰዎች ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስቴሯ አንደኛው ተጠቂ ከዱባይ መጥቶ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግለት የነበረ የ22 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ የአዲስ አበባና የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ የ52 ዓመት ሴትና ወንድ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በአራተኝነት የተመዘገበችው የ23 ዓመት በአማራ ክልል የአዲስ ቅዳም ነዋሪ ስትሆን ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ግንኙነት ስለመኖሩ እየተጣራ መሆኑን ከመረጃው መገንዘብ ተችሏል።