አይቆምም ዘፈኑ || በእውቀቱ ስዩም

አይቆምም ዘፈኑ || በእውቀቱ ስዩም

የመከራ ሰርዶ
የመከራ ተክል
አንድ ርምጃ ሲሳብ፤ አምሳ መሰናክል
ሲገጥመው የኖረ
ጨርሶ መክሰምን፤ በትግሉ የሻረ
ሰው የፍጥረት ቁንጮ፤ የተሰጥዖ ሀብታም
እንደ ያሬድ ትል ነው፤ ጨርሶ አይረታም::

ቢወድቅ፤ ክንብል ቢል
ከዘመን መዳፍ ላይ
መች ሊፈርጥ እንደ እንቡዋይ
እድሜውስ መች አጥሮ
በተስፋ ገንትሮ
በኑሮ
ጠጥሮ
ይነሳል ከምድር፤ እንደ ጎማ ነጥሮ::

የሞት ቀንዳም ፈረስ
ላዩ ላይ ቢሰግር
ለያንዳዱ ጣጣ
ብልሃት ቢቸግር
መፍትሄ ቢታጣ
ደሞ ሲደርስ ቀኑ
ለተዘጉ በሮች
መበርገጃ ቁልፎች
ግልጥልጥ ይላሉ፤ ዛሬ ቢዳፈኑ
ባንቀልባ ይተካል፤ የዛሬው ከፈኑ
ህይወት ማህሌታይ
ቴፑ ተሰባብሮም፤ አይቆምም ዘፈኑ::

LEAVE A REPLY