ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአፍሪካ ኅብረት ለአባል ሀገራቱ አንድ ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ገለፀ።
የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያዎችና መከላከያ ማዕከል cdc ለአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ የሚውል አንድ ሚሊዮን ኪት በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚያከፋፍል ይፋ አድርጓል።
በአህጉሩ ኅብረት ማዕከል አማካይነት የሚደረገው የኪት (የመመርመሪያ መሣሪያ) ድጋፍ የአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣትን ተከትሎ የገጠማቸውን የመመርመሪያ መሣሪያ እጥረት ተከትሎ የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ ታስቦ እንደሆነም ታውቋል: