ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ የፋሲካ በዐልን ምክንያት በማድረግ ለዐቅመ ደካሞች ዛሬ ስጦታ አበርክተዋል::
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አምባሳደር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመገኘት ነው ለዐቅመ ደካሞቹ ስጦታውን ያበረከተው::
ባለሥልጣናቱ በዐቅመ ደካሞቹ ወገኖቻችን ዘንድ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የበግ ፣ ዱቄቴና የዘይት ምርቶችን ለተረጂዎች በስጦታ አበርክተዋል::
በተያያዘ ዜና ሁለቱ አመራሮች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ለሚገኙ ከ50 በላይ ለሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች የግብዐት ድጋፍ አድርገውላቸዋል::