ኮሮና በአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ ስላሳደረው ተፅዕኖ ጥናት ተጀመረ

ኮሮና በአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ላይ ስላሳደረው ተፅዕኖ ጥናት ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች  ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናት እየተካሄደ ነው ተባለ።

በቫይረሱ  ስርጭት ምክንያት ሰዎች የዕለት ምግቦችንና የፅዳት እቃዎች ላይ በፍላጎት በኩል በከፍተኛ ደረጃ ማዘንበላቸውን ጥናቱን እያካሄደ ያለው የፌደራል አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ባለሥልጣን አስታውቋል።

ኅብረተሰቡ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ምርት ያለው ፍላጎት ቀንሷል፣ ይህንን ተከትሎ ቫይረሱ በቀጣይ በዘርፉ ሊያሳድረው ስለሚችለው ተፅዕኖ ጥናት እየተካሄደ ይገኛል ሲል ተቋሙ አስታውቋል።

ጥናቱ በዘርፉ ሊደረግ የሚገባውን ድጋፍ ያካተተ ነው የሚለው መግለጫ  የታክስ እፎይታ፣ የብድር ጊዜ ማራዘምና የተጨማሪ ብድር ጥያቄ  በጥናቱ ውስጥ ቅድሚያና ትኩረት እንዲሰጣቸው ተደርጓል ብሏል።

በኢትዮጵያ  ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያላቸው 19 ሺኅ የሚጠጉ አነስተኛ እና  መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እንደሚገኙና ከግማሽ ሚሊዮን ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ እድል እንደፈጠሩም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY