ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዛሬ ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሦስት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ396 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሦስት ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ እንደተገኘባቸውና ሦስቱም ሰዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተነግሯል።
ከሦስቱ የዛሬ ተመዝጋቢዎች መሀል የ11 ዓመት እና 15 ዓመት ታዳጊዎች ከጅቡቲ በለይቶ ማቆያ ተቀምጠው የነበሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፤ አንደኛው የ18 ዓመት ወጣት ግን የጉዞ ታሪክ የሌለው ተብሎ ቢመዘገብም ቆይቶ በተደረገ ማጣራት ከጅቡቲ የመጣና ለይቶ መቆያ የነበረ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር መስሪያቤት መረጋገጡን አስታውቋል።
በአሁኑ ሰዐት በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 111 ደርሷል:: 16 ሰዎች ሲያገግሙ አንድ በፅኑ ህሙማን ፣ 91 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማቆያ ክፍል ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።