የኮሮና ቫይረስን አምጣ የወለደችው ቻይና ወላጅነቷን እንደ መካድ የሚያደርጋት ነገር፡፡ የቫረሱን ስም እንኳን የቻይናው አውራ ፓርቲ CCP ከቻይና ዶክተሮች ጋር “ቫይረሱ አለ ይባል ይደበቅ?” በሚል ሲነታረክ የሰሙትን አፍሪካዊያንን እንደ ቫይረሱ ባለቤት በመቁጠር የምታዋክበው ነገር ኮሚኒዝምና ፕሮፖጋንዳ እንዴት እንደሚፋቀሩ የሚያስመሰክር ነው፡፡ይብስ የሚገርመው በቻይናው “Road and Belt Initiative” አፋቸው የታሸገው የአፍሪካ መሪዎች ስለዚህ ጉዳይ ምንም ማለት አለመቻላቸው ነው፡፡
“የኢትዮጵያ ባል,የኢየሩስዓሌም እጮኛ ነኝ” ሲል ኢየሩሳሌምን የማስገበር ህልሙን በጥበብ ሲናገር የነበረውአፄ ቴድሮስ፣ ህዝቡም ይህ ገብቶት “የካሳ ፈረሶች እጅግ ያሽካካሉ ከእየሩስዓሌም ጨፌ መጋጥ ይጓጓሉ” ሲልለት የነበረው፣ ኢትዮጵያን አልፎ መካከለኛው ምስራቅን ያማትር የነበረው፣ የዓይነ-ሰፊው መይሳው ካሳ የትውልድ ሃገር “ቡልጋ ነው ቆላድባ፣የለም ጎዛምን ነው፣አይደለም ላኮመልዛ ነው” እየተባለ ሲያነታርክ መክረሙ! ይህን ነገር መይሳው ቀና ብሎ ቢያይ “ለካ በዚህ ዘመንም ብወለድ “ከዘመኑ ቀድሞ የተወለደ” መባሌ አይቀርም ነበር ማለት ነው” ባይል ነው!
የልማታዊ ጋዜጠኝነት ታማኝ አገልጋይ(ነው ተገልጋይ?) አቶ ታደሰ ሚዛን “hibernate” ካደረገበት ብቅ ብሎ ትግራይ ሚዲያ ሃውስ ለሚባለው ሚዲያ ኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች የሚባሉ ሁለተኛ ዜጎችን ፈብርኮ የነበረው እነዚህ ክልሎች የትጥቅ ትግል “taste” ስላልነበራቸው ነው ሲል ማንም ካድሬ ገልፆት የማያውቀውን “Epistemology Construct” ማድረጉ፡፡ታደሰ ሚዛን በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን ሃገር የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ ነው….. ኢህአዴግ እናት ድርጅት ነው፤ሰው በስልጣን እና ሃብት ብቻ አይኖርም ሲል ትምህርትም ለካድሬዎቹ እንደ ፍላጎትና አቅማቸው ያቀርባል……
ለWHO ዋናነት ከነጥቁርነታቸው የተሾሙት ሰውየ “ዛሬ የሚወቀሱት ጥቁር ስለሆኑ ነው” ሲባል የምሰማው ነገር! ነው ሲሾሙ የቦሪስ ጆንሰንን ቆዳ ተውሰው ነበር? “ትግራይን ለማንበርከክ ነው” አለመባሉም ጥሩ ለውጥ ነው…
ከ “Quarantine” ጠፍተው የሚወጡ ሰዎች፤ እንዲወጡ የሚያግዙ ጠባቂዎች…. ምን ያለ ጠላታቸውን አግኝተው ሊጠመጠሙበት ይህን እንደሚያደርጉ ይገርመኛል!
“ሰው ገዳይ ነሽ አሉ ስሰማ ዝናሽን፣
ካሁኑ ፈራሁሽ እኔን አደራሽን” ያለው ሙሉቀን ወዶ ነው? እኔን አደራቸውን