በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎች አያያዝ ምን እንደሚመስል በመርማሪ ቦርድ ተጎበኘ

በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎች አያያዝ ምን እንደሚመስል በመርማሪ ቦርድ ተጎበኘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ዜጎች ሀኔታና አያያዝ ምን እንደሚመስል የሚያጣራ ቡድን በዛሬው እለት ጉብኝት አደረገ።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተቋቋመው መርማሪ ቦርድ፤ በለይቶ ማቆያው የሚገኙ ዜጎች አያያዝ የሰብአዊ መብትን ያከበረ መሆኑን ለማረጋገጥ ምልከታ አድርጓል ነው የተባለው፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመቆጣጠርም በተመሳሳይ ቦርዱ ክትትል ማድረግ መጀመሩን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ጽ/ ቤት አስታውቋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ቢፈፀሙ ተከታትሎ ለህግ የማቅረብ ሓላፊነት የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል።  ቦርዱ የምርመራ ውጤቱንም ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የማቅረብ ግዴታም እንዳለበት ተደንግጓል።

LEAVE A REPLY