ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የቆየ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ።
የቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ሓላፊ ዋና ሳጅን ዳምጠው ሞላ እንደገለፁት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓም ከምሽቱ ሦስት ሰዐት ላይ በወረዳው “ነብስ ገበያ ቁጥር አንድ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፣ የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ ሲንቀሳቀስ ነው ።
የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪው የሰሌዳ ቁጥር በሌለው ሞተር ሳይክል ይዞ እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ወቅት ፤ 1 ሺህ 142 የክላሽንኮቭና 500 የብሬን ጥይቶች ፣ እንዲሁም 38 የክላሽካዝናዎች ይዞ ነበር ተብሏል።
ተጠርጣሪው የተያዘበት ወረዳ ከሱዳን ጋር የሚዋሰን በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በወጣው አዋጅ መሰረት የፀጥታ አካላት ቁጥጥር በሚያደርጉበት ወቅት እንደተያዘ ሰምተናል።