ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኦሮሚያ ክልል የተለያዮ ከተሞች የንግድ ሱቆቻቸው ታሽጎ የቆዮ ከ4 ሺኅ በላይ ሱቆች ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸው ተነገረ።
ሱቆቹ ከአንድ ወር በላይ ታሽገው የቆዮት የኮሮና ቫይረስን አስታከው ያልተገባ ጭማሪ በሸቀጦች ላይ በማድረጋቸው እንደነበር ይታወሳል።
ነጋዴዎቹ ከክልሉ መንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ የፈፀሙት ተግባር ስህተት መሆኑን ከማመናቸው ባሻገር ለመታረም ዝግጁ ነን በማለታቸው ታሽጎ የነበረ ሱቃቸው ሊከፈትላቸው እንደቻለ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሓላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ገልጸዋል።
2,300 የሚሆኑ ከረምቡላና ሺሻ ቤቶች፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች፣ ባህላዊ መጠጥ ቤቶች (አረቄ፣ ጠጅና ጠላ መሸጫዎች) በቀጣይም ተዘግተው እንደሚቆዮ ተረጋግጧል። እነዚህ ቤቶች ዝግ የሚሆኑት ቢከፈቱ ለኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምቹ አጋጣሚ ይፈጥራሉ በሚል ነው መባሉን ተነግሯል።
በተጨማሪም 56 ነጋዴዎች ጉዳያቸው በሕግ እየታየ መሆኑን፣ የተለያዮ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ የተያዙ 5600 ነጋዴዎች ደግሞ በማስጠንቀቂያ መተላለፋቸውን የክልሉ ንግድ ቢሮ ይፋ አድርጓል።