ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።
በተጠቀሰው 24 ሰዐታት ውስጥ ለ965 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጓል ነው የተባለው። ሰሞኑን ተደጋጋሚ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ተከትሎ በዚህ ምርመራ በኅብረተሰቡ ተመሳሳይ ነገር ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም አንድም የኮቪድ 19 ታማሚ የሆነ ሰው አልተገኘም::
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ይፋ ባደረጉት መረጃ ላይ በ24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገው ምርመራ ቫይረሱ የተገኘበት ሰው አለመኖሩን አረጋግጠው ፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 116 መሆኑን ፣ከእነዚህ ውስጥ 90 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ እንደሚገኙና በአንፃሩ 21 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን ገልጸዋል።