በደሴ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ዛሬ ተጀምሯል

በደሴ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ዛሬ ተጀምሯል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሳሳቢ ደረጃ የደረሰውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በደሴ ከተማ  የቫይረሱ ምርመራ ከዛሬ  ጀምሮ  እንደሚካሄድ ታወቀ፡፡

የምርመራ ማዕከሉ በአንድ ቀን ውስጥ 300 ናሙናዎችን የመመርመር አቅም አለው ተብሎለታል፡፡ መገናኛ ብዙኃኑ የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የደሴ ከተማ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ምሳዬ ምርመራውን የሚያካሂዱ ባለሙያዎች ሥልጠናቸውን አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ በደሴ ከተማ አስተዳዳር ፣ ደቡብ ወሎ ዞን እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡ በአማራ ክልል የባህርዳርና የጎንደር መመርመሪያ ማዕከላት አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በሌሎች የክልሉ ከተሞች የምርመራ ማዕከላትን ለማስፋፋት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ ታሪኩ በላቸው ለቢቢሲ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

LEAVE A REPLY