ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ኮሮና ቫይረስ የፈውስ መላዎች የሰጡት አስተያየት የጤና ባለሙያዎችን አስቆጣ፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለበሸታው ፈውስ የረቂቅ ተሕዋስያን ማጥፊያ ዲስ ኢንፌክታንት ኬሚካል በመርፌ የሚሰጥበት ምርምር እንዲደረግ ሓሳብ ማቅረባቸው የጤና አዋቂዎችን ስሜታዊ አድርጎ በእጅጉ ማስቆጣቱ በስፋት እየተዘገበ ይገኛል፡፡
የዶናልድ ትራምፕን ሐሳብ ውድቅ ያደረጉትና የፕሬዝዳንቱን አላዋቂነት በማንሳት ክፉኛ ያብጠለጠሏቸው የሕክምና ኤክስርቶች ዲስ ኢንፌክታንት (ኬሚካል) ወደ ሰውነት ከገባ አደገኛና መራዥ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ተመሳሳይ በሆነ መልኩ አንድ የዋይት ሀውስ ሹም “የፀሐይ ጨረርም ለኮሮና ቫይረስ ፍቱን ነው” ሲሉ መናገራቸው የጤና ሊቃውንት ድፍረት የተሞላበት አስተያየት ነው በሚል እየተተቸ መሆኑንም እየተመለከትን ነው፡፡ ሐኪሞቹ የትራምፕ ሐሳብ ሥራ ላይ ይዋል ከተባለ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ሲሉ ከወዲሁ አስጠንቅቀዋል።