አየር መንገዱ ያጣውን ገቢ የጭነት ጉዞዎችን በመጨመር ለእየሠራ መሆኑን ተገለጸ

አየር መንገዱ ያጣውን ገቢ የጭነት ጉዞዎችን በመጨመር ለእየሠራ መሆኑን ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኮሮና ቫይረስ ቻይና ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ወቅት ጊዜ አየር መንገዱ ወደ ስፍራው ሲያደርግ የነበረውን በረራ አለማቋረጡ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር ሲሉ ገለፁ።

በንግድ ግንኙነት ምክንያት ከቻይና ጋር ጥብቅ ቁርኝት ላላቸው የአፍሪካ አገራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወሳኝ አገልግሎት ሰጥቷል ያሉት አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ፤ አየር መንገዳቸው በቀጥታ በረራና በኮቪድ-19 ስርጭት መካከል ግንኙነት አለው ብሎ እንደማያምን ከመጠቆማቸው ባሻገር ጠበቅ ያለ የጉዞ ቁጥጥርና እገዳዎችን ባወጡ አገራት ውስጥ ሳይቀር ወረርሽኙ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነም አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይና ውስጥ በሽታው ተስፋፋፍቶ በነበረበት ወቅት ቤይጂንግና ሻግሃይን ወደመሳሰሉ ከተሞች በረራ ያደርጉ ከነበሩ የተወሰኑ አየር መንገዶች መካከል አንዱ  ነው:: በሽታው በመላው ዓለም ከተሰራጨ በኋላ ክፉኛ ተጽዕኖውን ካሳረፈባቸው ዘርፎች መካከል የአየር ትራንስፖርት አንዱ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድም ከፍ ያለ ኪሳራ አላጋጠመውም ተብሏል። አየር መንገዱ በአሁኑ ጊዜ ካለው አቅም በ10 በመቶ ብቻ እየሰራ መሆኑን ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማጣቱን ሮይተርስ በቅርቡ መዘገቡም ይታወሳል።

አቶ ተወልደ የአየር ትራንስፖርት ዘርፉ በወረርሽኙ ምክንያት የገጠመውን ፈተና በተመለከተ ለቢቢሲ ሲያስረዱ ፣ድርጅታቸውን በዚህ የቀውስ ወቅት ይዞ መራመድ ፈታኝ ቢሆንም ጭነት በረራዎችን በመጨመር፣ በመንገደኞች ጉዞ ያጣውን ገቢ ለማካካስ እየሞከረ መሆኑን ጠቁመዋል።

 

LEAVE A REPLY