ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በቤይሩት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምግብና የመጠለያ እርዳታዎች እንዲቀርብላቸው የኢትዮጵያ መንግሥትመጠየቁን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ከዓመት በፊት በሊባኖስ የተከሰተው የምጣኔ ሀብት ቀውስ በቤይሩት በሚኖሩ ዜጎች ላይ ጫና ማሳደሩን ያሳደረ ሲሆን፤ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በአገሪቱ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ደግሞ በተጨማሪ የአገሪቱን የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ ከትቶታል ነው የተባለው፡፡
በዚህ ችግር የተነሳ በቤይሩት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዘላቂነት ከአገሪቱ ለማስወጣት የመንግሥት እገዛ እንደሚያሻ በስፍራው የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ አስታውቋል፡፡
“ስለ ጉዳዩ በአገር ቤት ለሚገኙ የሚመለከታቸው ተቋማት አሳውቄያለሁ “ያለው ቆንስላው የሚመለከታቸው አካላት ችግሮቹን የሚፈቱበትን መንገድ እያማተሩ መሆኑንም እግረ መንገድ እንድታውቁልኝ እሻለሁ ብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በቤይሩት ከ400 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ ተብሎ ሲገመት ፤ አብዛኞቹ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው፣ ሰነድ አልባ ዜጎች መሆናቸው በመነገር ላይ ነው፡፡