በኒው ዮርክ ከተማ አንዲት ዶክተር ራሷን አጠፋች

በኒው ዮርክ ከተማ አንዲት ዶክተር ራሷን አጠፋች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዓለምን እያስጨነቀ ባለው የኮሮና ቫይረስ  በከፍተኛ ሁኔታ በተጠቃችው የአሜሪካዋ ኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ ትሰራ የነበረች ዶክተር እራሷን ማጥፋቷ ተሰማ።

ሟቿ ዶክተር ሎርና በሬን ኒው ዮርክ ማንሀተን ውስጥ በሚገኘው ” ፕሪስቢቴሪያን አለን” ሆስፒታል ውስጥ የድንገተኛ ክፍል ሜዲካል ዳይሬክተር ነበረች:: ዶክተሯእሁድ እለት እራሷ ላይ ባደረሰችው ጉዳት ህይወቷ እንዳለፈ ፖሊስ ሲገልጽ ፣ አባቷ ዶክተር ፊሊፕ በሬን ደግሞ “ሥራዋን ለመሥራት ስትጥር ቆይታለች ነገር ግን ሥራዋ ለዚህ አበቃት” ሲሉ ለኒዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።

አሜሪካ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሞቱት 56 ሺህ ሰዎች ውስጥ 17.500 ያህሉ የሚገኙት በኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ ነው። የዶክተሯ አባት ልጃቸው ከዚህ በፊት ለዚህ ሊያበቃት የሚችል የአዕምሮ ህመም አልነበረባትምብለዋል።

ዶክትር ሎርና የህክምና ሥራዋን በምታከናውንበት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ ተይዛ ታማ የነበረ ሲሆን፤ ለአንድ ሳምንት ከግማሽ እራሷን ለይታ ካቆየች በኋላ አገግማ ወደ ሥራዋ መመለሷንም ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY