ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አንድ ሺኅ ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረ የቤተክርስቲያን ግድግዳ በኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ተነገረ:: ግኝቱን የደረሱበትና ይፋ ያደረጉት የፖላንድ ባለሙያዎች ናቸው።
በዋርሶው ዩኒቨርስቲ የፖላንድ የሥነ ቁፋሮ ሳይንስ ማዕከል ባለሞያዎች እድሜ ጠገቡን የቤተ ክርስቲያን ያገኙት በቁፋሮ መሆኑም ታውቋል።
የጥናት ቡድኑ አባላት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ባለፈው መጋቢት ወር ውስጥ ሲያከናውኑት የነበረውን ቁፋሮ ለማቋረጥ ተገዶ ነበር።
ይሁን እንጂ ከቀናት በፊት በአነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላን ባደረገው ቅኝት ደብረ ገርጊስ ቤተ መቅደስ (የጊዮርጊስ ገዳም) የተሰኘ ረጅም ቁመት ያላቸው በርካታ ምሰሶዎች ያሉት የመካከለኛው ዘመን ቅሪት በኢትዮጵያ ውስጥ ማግኘቱን ዛሬ ለዓለም አስታውቋል።
በኢትዮጵያ ረጅም ዓመታት የሥነ ቁፋሮ ልምድ ያላቸው ጣልያናዊቷ የግኝት ቡድኑ መሪ ዶክተር ሚቼላ ጋውዴሎ “የአካባቢው ነዋሪዎች በስፍራው ጥኔታዊ ቤተ ክርስቲያን ቤተ መቅደስ መኖሩን ቢያውቁም መቼ እንደተገነባና ምን እንደሚመስል አያውቁም” ብለዋል።
በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ሰው አልባ አውሮፕላን በተደጋጋሚ በመጠቀም ረገድ የመጀመሪያው የሥነ ቁፋሮ ቡድን መሆኑንም ዶክተር ሚቼላ ተናግረዋል።