ዛሬ በአዲስ አበባ ሁለት እንግሊዛውያን የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ዛሬ በአዲስ አበባ ሁለት እንግሊዛውያን የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዛሬ ሚያዚያ 20 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ1 ሺህ 80 ሰዎች ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራ መደረጉን  የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ በተደረገው ምርመራም ተጨማሪ 2 ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ እንደተገኘባቸውና ይህንን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 126 መድረሱን አብራርተዋል።

በዛሬው ዕለት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁለቱም ሰዎች የ42ዓመት እድሜ እና የ50 ዓመት እድሜ ያላቸው የብሪታኒያ ዜጎች እንደሆኑ፣ ግለሰቦቹ በቅርቡ ከብሪታንያ መጥተውበአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የቆዩ እንደነበሩ አረጋግጠዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 126 ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 71 ሰዎች በለይቶ ህክምና ውስጥ ሲገኙ፤ 50 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል።

LEAVE A REPLY