በጅግጅጋ ሦስት ወጣት ሴቶች ፣ አንድ ወንድ በሐረር የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

በጅግጅጋ ሦስት ወጣት ሴቶች ፣ አንድ ወንድ በሐረር የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፉት ሀያ አራት ሰዐታት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ766 ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ አራቱ የኮሮና ቫይረስ እንደ ተገኘባቸው ተነገረ።

የጤና ሚኒስትሯ፣ ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት፤ ዛሬ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል የ15፣ የ18 እና 25 ዓመት ታዳጊና ወጣት ሴቶች ከፑንትላንድ የተመለሱ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ባለው የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አስታውቀዋል።

አራተኛው ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የ23 ዓመት ወጣትና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ “ጉባ ኮሪቻ ” ወረዳ  ውስጥ ነዋሪ እንደሆነም ተነግሯል።

ወጣቱ ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ የሌለው በመሆኑ፤ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ስላለው ግንኙነት ማጣራት እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 58 መድረሱን አረጋግጠዋል።

LEAVE A REPLY