የታከለ ኡማ አስተዳደር የድሆችን ቤት እያፈረሰ መሆኑን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋግጫለሁ አለ

የታከለ ኡማ አስተዳደር የድሆችን ቤት እያፈረሰ መሆኑን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አረጋግጫለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዓለም ዐቀፉ የሰብኣዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢነተርናሽናል በኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የቀን  ሠራተኞች እና ሥራ አጥ የሆኑ፣ የድሃ ሰዎችን መኖሪያ ቤታቸውን አፍርሷል ሲል አስታወቀ።

በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ በተወሰደ እርምጃ የፈረሱት መኖሪያዎች ወረርሽኙን ተከትሎ የዕለት ገቢያቸውን አጥተው የተቀመጡ ሰዎች ቤቶች እንደሆኑም ከነዋሪዎች ጠይቆ መረዳቱን  አምንስቲ ገልጿል።  በተጨማሪም መኖሪያቸው የፈረሰባቸው ሰዎች በሜዳ ላይ እንደሚገኙ፣ ከሕግ አስከባሪዎች በሚደርስባቸው ወከባ፣ እንዲሁም ከዝናብ ለመጠለል በሚቀልሱት የላስቲክ መጠለያንም እያፈረሱባቸው በመሆኑ፤  ሁሉንም ሌሊቶችን ያለ ዕንቅልፍ እንደሚያሳልፉ መግለጫው ይፋ አድርጓል።

በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር ዴፕሮስ ሙቸና፤ መጠለያቸው የፈረሰባቸው ሰዎችና ሕጻናት ልጆቻቸው ለዝናብ እና ለብርድ እንደተዳረጉ ጠቁመው፤ “ነዋሪዎቹም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከወረርሽኙ ሊተርፉበት የሚችለው መንገድ በቤት ውስጥ በመቀመጥ ቢሆንም፣ የመኖሪያቸው መፍረስ ለወረርሽኙ ተጋላጭነታቸውን ያሰፋዋል” ብለዋል።

ኢንተርናሽናል የሰብኣዊ መብት ተሟጋቹ (አምንስቲ) ከቦሌክፍለ ከተማ ሥራ ሓላፊዎች አገኘሁ ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው በሕገ ወጥመንገድ የተገነቡ መኖሪያዎች መፍረሳቸውን ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ መኖሪያቸው የፈረሰባቸው ግለሰቦች ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ከገበሬዎች መሬቱን በመግዛት፣ መኖሪያውን ሠርተው መኖር እንደጀመሩ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል በዝርዝር አስቀምጠዋል።

LEAVE A REPLY