ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ ባለፉት በ24 ሰዐታት ውስጥ ለ1 ሺኅ 408 ሰዎች በላብራቶሪ የታገዘ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ ።
በዚህ ምርመራ ተጨማሪ አንድ ሰው ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱንም ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰብ ኢትዮጵያዊ ሴት ፣ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ናቸው:: ግለሰቧ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደሆኑም ተሰምቷል።
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 131 መድረሱን የጠቆሙት ዶክተር ሊያ ታደሰ፤ ከትናንት እሰከ ዛሬ ባለው የ24 ሰዐታት ውስጥ ተጨማሪ አንድ ሰው ከቫይረሱ ማገገሙን አስታውሰው፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 59 መድረሱንም ይፋ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘ ጀምሮ የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ ሁለት ሰዎች ደግሞ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።