አስቸኳይ አዋጁ በኦሮሚያ ክልል በትክክል እየተተገበረ አይደለም ተባለ

አስቸኳይ አዋጁ በኦሮሚያ ክልል በትክክል እየተተገበረ አይደለም ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመቆጣጠር ሲባል የወጣው የአስቸኳይ አዋጅ በኦሮሚያ ክልል ወጥ በሆነ መንገድ እየተተገበረ አለመሆኑ ተነገረ::

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች  አመራር አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ባልቻ በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች በፀጥታ ኃይሎችም በኩል ወጥነት የጎደለው አሠራር እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል::

ሰሞኑን በተካሄደ ሰፊ ጥልቅ ስብሰባ በኋላ በሁሉም ስፍራዎች ሕጉ በትክክልና በተገቢው መንገድ እንዲተገበር ትዕዛዝ መተላለፉን የጠቆሙት አቶ ጌታቸው ባልቻ ፣ የፀጥታ ኃይሎችም ከሚቀርብባቸው ትችት በፀዳ መልኩ ሥራቸውን እንዲሠሩ መወሰኑን አብራርተዋል::

“የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የወጣው የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ለማሰር ሆን ተብል  ነው” በማለት የሚከራከሩ አሉ የሚሉት ጌታቸው ባልቻ የኮሮና ቫይረስን መከላከል ከፖለቲካ በላይ ስለሆነ  የፖለቲካ ፓርቲዎቹ  ጉንጭ አልፋ ከሆነ ክርክር ይልቅ ቫይረሱን ለማጥፋት መሥራት አለባቸው ሲሉ እንደ ኦነግና ኦፌኮ ያሉትን ወቀሳ አቅራቢ ፓርቲዎች ተችተዋል::

LEAVE A REPLY