ፖሊስ የወሰደውን የእስክንድር ነጋ ስልክ እንዲመልስ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ

ፖሊስ የወሰደውን የእስክንድር ነጋ ስልክ እንዲመልስ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ቅዳሜ ዕለት አስቸኳይ አዋጁን ተላልፈኻል በሚል ለእስር ተዳርጎ የነበረውና ምሽት ላይ የተለቀቀው የባልደራስ ፓርቲ ሊቀ-መንበር  የአቶ እስክንድር ነጋ ስልክን ፖሊስ በአፋጣኝ  እንዲመልስ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አሳሰበ።

ዓለም ዐቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ የእጅ ስልክ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖሊስ ቊጥጥር እንደሚገኝ ባወጣው መግለጫ ላይ አስታውሶ፤ አቶ እስክንድር ኮሮናን ለመከላከል የወጣውን አካላዊ መራራቅ (ማኅበራዊ መራራቅ) ደንብ ሳይጥሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ስልካቸውን ወስዶባቸዋል ሲል የፖሊስን አሠራር ተችቷል

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪቃ ክፍል በትዊተር ማኅበራዊ መገናኛ ይፋዊ ገጹ ላይ ዛሬ ባሰፈረው ጽሑፍ “አቶ እስክንድር ነጋ ለዲጂታል ደህንነታቸው ሥጋት ገብቷቸዋል፤ ፖሊስ የእጅ ስልካቸውን ከፍቶ ሙሉ ለሙሉ እንደፈለገ ማድረግ መቻሉንም ተናግረዋል” ሲል አስፍሯል።

ፖሊስ ስልኩን በአፋጣኝ ለባለቤቱ እንዲመልስ  ያሳሰበው አምነስቲ፤ ፖሊስ ኮቪድ 19ኝን ሰበብ አድርጎ የሰብአዊ መብታቸውን ከመጣስም ይቆጠብ በማለት አስጠንቅቋል::

LEAVE A REPLY