አስከፊ ወረርሽኝ ዓለምን ባስጨነቀበት በዚህ ወቅት፣ ቤት በላያቸው ላይ የሚፈርስባቸውን ወገኖች በማሰብ
ቆዳው ሞኛሞኝ – ስልቱ የረቀቀ፣
“ጽድቅና ኩነኔው” – የተደባለቀ፤
“ታቦት አስረክሶ” – ልቤተስኪያን መስሪያ
መሬት እሚመትር፣
ሕጻናት አጥግቦ – ጎዳና እሚያሳድር፤
ክቡር ነፍስ አስጠፍቶ – ሃዘን እሚቀመጥ፣
ቀድሞ ለቅሶ ደራሽ – የእዝን ተስፋ እሚሰጥ፤
ጨለማን ተግኖ – በጓዳ እሚነቅል፣
በብርሃን አዋጅ – በ”ቲቪ” እሚተክል፤
ለፍርድ ያስቸገረው – ማን ይባል ይሄ ሰው?
ቀን የገነባውን – ሌሊት እሚያፈርሰው!
ሚያዝያ 2012 ዓ/ም
አፕሪል 2020)