ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ሕይወት የተቀናጀ የልማት ድርጅት ከሠራተኞቹ፣ ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ እና ከበጎ ፈቃደኞች የሰበሰበውን ከ600 000 (ስድስት መቶ ሺኅ) ብር በላይ ለተቸገሩ ዜጎች ማከፋፈሉን አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ያገኘውን 183.060 ብር፤ ለ204 (ሁለት መቶ አራት) ወላጆቻቸውን ላጡ ታዳጊዎች ድጋፍ ማድረጉን ጠቁሞ፤ ለተመሳሳይ ዓላማ ከሠራተኞቼ የሰበሰብኩትን 120,000 ብር በሦስት ክፍለ ከተሞች ለተቸገሩ ዜጎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ መግዢያ እንዲያውሉት አስረክቤያለሁ ብሏል፡፡
የልማት ድርጅቱ በቀጣዮቹ ቀናትም 200 ለሚሆኑ ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስድጋፍ ለማድረግ መሰናዶውን እንዳጠናቀቀ ይፋ አድርጓል።