ባልደራስ ፓርቲ “የባለሙያዎች ባለአደራ መንግሥት” እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበ

ባልደራስ ፓርቲ “የባለሙያዎች ባለአደራ መንግሥት” እንዲቋቋም ሐሳብ አቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ ትናንት እና ዛሬ ሲያካሂድ በቆየው ስብሰባ ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ችግር መፍትኄ ይሆናሉ ያላቸውን ሐሳቦች ላይ ከስምምነት ደርሶ ውሳኔ ማሳለፉን ገለፀ::

ፓርቲው ሚያዚያ 24 እና 25 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ሀገራችን ባጋጠማት ተግዳሮት ላይ አዲስ የውሳኔ ሀሳብ ማግኘቱንና ፤ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፣ የሥልጣን ዘመኑ ሲያበቃ ቀጣዩን ጊዜ በተመለከተ ጠንካራ አማራጭ ሐሳብ  ነው ያለው ዕቅዱን ለመንግሥት ማቅረቡን አስታውቋል።

በእስክንድር ነጋ የሚመራው የባልደራስ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህን አማራጭ ሐሳብ ሲያቀርብ፣ በቅድሚያ የሀገራችንን ዘላቂ ጥቅም፣ ሠላምና ደህንነት ብቻ ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ነገ ዘጋቢ አስታውቋል።

ከሲቪክ ማኅበርነት ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ከተሸጋገረ ገና በቅጡ የመንፈቅ ጨቅላ ሕፃን እድሜ ያልሞላው የባልደራሱ ፓርቲ ከመኢአድ ጋር የፈጸመውን ውህደት ተከትሎ ፣ እንዲሁም በዋና መዲናዋ ፣ በባህርዳርና እና በጎንደር ከተሞችያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች ተከትሎ በሕዝብ ዘንድ ድጋፍም ተቃውሞም  እያስተናገደ ይገኛል::

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው “የባለሞያዎች ባለአደራ መንግሥት” ወይም በእንግሊዘኛ አጠራሩ “Care Taker Government of Techonocrats” ማቋቋም ወቅቱን ከግምት ውስጥ ያስገባ እውነተኛ መፍትኄ እንደሆነ በሙሉ ድምፅ  መወሰኑን ለኢትዮጵያ ነገ ጠቁሞ ፤ የአማራጭ ሐሳቡንዝርዝር ነገ ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም  ለሕዝብና ለሚዲያ አካላት ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

LEAVE A REPLY