የጉዞ ታሪክ ሳይኖራቸው 5 ወጣቶች በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

የጉዞ ታሪክ ሳይኖራቸው 5 ወጣቶች በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ሳይኖራቸው የኮሮና ቫይረስ የሚገኝባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሯ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸውና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ሳይኖራቸው በቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ መዘናጋት እንደማይገነባ ጠቁመው፤ ኅብረተሰቡ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር “አነስተኛ ነው” በማለት መዘናጋቱ እንዳስጨነቃቸው ገልፀዋል።

በጎረቤት አገራት በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ  መሆኑ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ዶክተር ሊያ ታደሰ፤ ሳይንሳዊ ምርምሮችም የቫይረሱ ስርጭትም ሊጨምር እንደሚችል እያሳዩ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ሳይዘናጋ ጥንቃቄ ማድረግ ተደጊ ነው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ1758 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አምስት ሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁት አምስት ሰዎች መሀል አራቱ ከ17 ዓመት እስከ 24 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው  ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ አምስተኛው ወጣት በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሲውድናዊ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY