ተዘግቶ የቆየው ግቢ በሸክላ ሥራ ለተሰማሩ እናቶች ተሰጠ

ተዘግቶ የቆየው ግቢ በሸክላ ሥራ ለተሰማሩ እናቶች ተሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በተለምዶ ናይጄሪያ ኤምባሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለረጅም ጊዜ ተዘግቶ የቆየ ግቢ በሸክላ ሥራ ላይ ለተሰማሩ እናቶች መሰጠቱ ታወቀ::

በአንድ በኩል ማኅበረሰባዊ ፋይዳ ያላቸው በጎ ሥራዎችን ሲያከናውን በሌላ ጎኑ በክፉ ወቅት ዜጎችን ሕገ ወጥ ናችሁ በማለት ከቤታቸው እያፈናቀለ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ “ግቢውን በሸክላ ሥራ ላይ ለተሰማሩ እናቶች ማምረቻና መሸጫ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ” ብሏል።

እናቶቹ ከዚህ ቀደም ሢሠሩበት የነበረው ቦታ ለ ሚያካሂዱት ሥራ የማይመች የነበረ ከመሆኑ አኳያ አዲሱ  ቦታ፣ ለእናቶቹ የመስሪያ ምቾት ከመፍጠሩ ባሻገር በተጨማሪም የገበያ ትስስር ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ተገምቷል።

እነዚህ ኑሯቸውን በዝቅተኛ ገቢ የሚገፉት እና በባህላዊ የሸክላ ሥራ የሚተዳደሩት የኅብረተሰብ ክፍሎች ተዘግቶ የነበረው ቤት የተሰጣቸው በጊዜያዊነት እንዲጠቀሙበት መሆኑን ከከተማ መስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የከተማው ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተረሱትን የህብረተሰብ ክፍሎች በማስታወስ ድጋፍ እንዲያገኙ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።

ም/ከንቲባው የተለያዩ በሽመና ሥራ የሚተዳደሩ አነስተኛ ጎጆ ኢንዱስትሪ እንዲያድጉና የተሻለ የሥራ ቦታ አግኝተው ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲረዱ ያስችላል ያሉትንም የመስሪያ ቤት ግንባታ ትናንት ማስጀመራቸው አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY