ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዓለም ዐቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ከሰሃራ በታች ለሚገኙ 24 የአፍሪካ ሀገራት በአጠቃላይ የሰጠው የብድርመጠን 9 ቢሊየን 539 ሚሊየን 17 ሺህ ዶላር መሆኑ ተሰማ:: ከብድሩ ውስጥ ሩብ ያህሉን በማግኘት ናይጄሪያ ከፍተኛውን ብድር የወሰደች ሀገር ሆናለች፡፡
አይ. ኤም. ኤፍ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ከድርጅቱየብድር መጠን በመውሰድ ቀዳሚ የሆኑት ዐሥር ዋና ሀገራትን በቅደም ተከተል ይህንን ይስላሉ:-
1. ናይጄሪያ 3.4 ቢልየን ዶላር
2. ጋና 1.0 ቢሊየን ዶላር
3. ኬንያ 739 ሚሊየን ዶላር
4. ኮትዲቯር 590.8 ሚሊየን ዶላር
5. ዩጋንዳ 491.5 ሚሊየን ዶላር
6. ኢትዮጵያ 411 ሚሊየን ዶላር
7. ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ 363.27 ሚሊየን ዶላር
8. ሞዛምቢክ 309 ሚሊየን ዶላር
9. ካሜሩን 226 ሚሊየን ዶላር
10. ማሊ 200 ሚሊየን ዶላር