ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍ ሰዎችን ሰብስበው ጠጅ ሲያጠጡ የተገኙት የጠጅ ቤት ባለቤት በገንዘብ ተቀጥተዋል ተባለ፡፡
ባለ ጠጅ ቤቱ፤ በጠባብ ክፍል ውስጥ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ፣ ለ14 ሰዎች መጠጡን ሲሸጡ መገኘታቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
በተለምዶ አውቶቡስ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተፈፅሟል የተባለው ይሄ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥሰትንየተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት። አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት፤ ጉዳዩን መርምሮ በግለሰቡ ላይ ማስተማሪያ ይሆናል ያለውን የ1.500 ብር የገንዘብ ቅጣት አስተላልፎባቸዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የወጣው መረጃ ስለጠጪዎቹ መቀጣትና አለመቀጣት አንዳችም ያሰፈረው ነገር አለመኖሩን መታዘብ ተችሏል፡