ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሲሚንቶ አምራች ኢንዱስትሪዎች በኮቪድ 19 ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጎዱ ዘርፎች አንዱ እንደሚሆን ተሰማ፡፡ የፌደራልና የክልል መንግሥታት በጋራ ዘርፉን በመደገፍ ከተጋረጠበት አደጋ መታደግ እንደሚጠበቅባቸውም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንደገለፀው ከሆነ ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ከፍ ያለ አስተዋፅኦ የሚያበረክተውን፣ ለብዙ ዜጎችም ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ እድል በመፍጠር ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚሰለፈውን የሲሚንቶ አምራች ኢንዱስትሪ ያለበትን ችግር እንዴት ማቃለል ይቻላል በሚለው ላይ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
የስፔር ፓርት፣ ዘይትና ቅባት፣ የውጭ ምንዛሬ፣ የማሸጊያ ማዳበሪያ፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ የድንጋይ ከሰል እጥረት እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ መናር የዘርፉ ችግሮች መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን ፣ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል አለመኖርና ፍልሰት የሲሚንቶ ኢንዱስትሪውን ዘርፍ አንቀው የያዙት ዋነኛ ችግሮች ናቸው ተብሏል፡፡