አምስተኛው ሰው ዛሬ ሕይወቱ አልፏል ፣ 16 ተጨማሪ ሰዎችም በኮሮና ተይዘዋል

አምስተኛው ሰው ዛሬ ሕይወቱ አልፏል ፣ 16 ተጨማሪ ሰዎችም በኮሮና ተይዘዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ ባለፉት 24 ሰዐት ውስጥ በተደረገው 2.383 (ሁለት ሺኅ ሦስት መቶ ሰማኒያ ሦስት) ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ፤ 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 210 እንደ ደረሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 97 ደርሷል ነው የተባለው።

በሌላ በኩል አንድ ሰው ዛሬ ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን አጠቃላይ በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፋ ሰዎች ቁጥር 5 ደርሷል። ዛሬ መሞቱ የተነገረው አምስተኛ ሰው ሰሞኑን በፅኑ ሕሙማን ክፍል ውስጥ የቆየ መሆኑ ታውቋል::

ዛሬ የኮቪድ 19 ቫይረስ ከተገኘባቸው አስራ ስድስት ሰዎች 13ቱ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ሢሆኑ፤ ሁለቱ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው:: አንደኛው ግለሰብ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸውና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መግለጫ ያሳያል::

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሢሆኑ ሰባት ወንድና ዘጠኝ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል:: ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት እስከ 60 ዓመት  የሆነው የቫይረሱ ተጠቂዎች፤ 13ቱ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ፣ አንድ በአማራ ክልል ወልዲያ ለይቶ ማቆያ፣ ሁለት በደቡብ ክልል በወላይታ ሶዶ እና ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተሞች የሚገኙ ናቸው ተብሏል::

LEAVE A REPLY