የአቶ ለማ መገርሳ ድምፅ እንዳይተላለፍ የተደረገበት ምክንያት እየተጣራ ነው ተባለ

የአቶ ለማ መገርሳ ድምፅ እንዳይተላለፍ የተደረገበት ምክንያት እየተጣራ ነው ተባለ

Office call in honor of His Excellency Lemma Mergesa, minister of defense, Democratic Republic of Ethiopia, hosted by Army Maj. Gen. Timothy Kadavy, special assistant to the chief of the National Guard Bureau, the Pentagon, Washington, D.C., Dec. 3, 2019. (U.S. Army National Guard photo by Sgt. 1st Class Jim Greenhill)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔት ዎርክ (ኦቢኤን) የቦርድ አባል እና የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ፤ የአቶ ለማ መገርሳ ድምጽ በኦ ቢ ኤን እንዳይተላለፍ ስለመደረጉ የሚያውቁት ነገር እንደሌለና ጉዳዩምእንደሚጣራ ገልጸዋል::

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሚተዳደረው የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት የሆነው ኦ ቢ ኤን ላይ የክልሉ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአገሪቱ የመከላከያ ሚንስትር የሆኑትየአቶ ለማ መገርሳን ድምጽ እንዳይተላላፍ ተደርጓል በሚል የድርጅቱ ጋዜጠኞች ቅሬታ እንዳሰሙ ኢትዮጵያ ነገ ትናንት ዘግቦ ነበር።

ረቡዕ እለት በአዳማ ከተማ በተፈጸመው የታዋቂው ባለሀብት በአቶ ከቢር ሁሴን ቀብር ላይ አቶ ለማ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር “ከላይ በመጣ ትዕዛዝ “በሚል በድርጅቱ ሓላፊዎች ድምጻቸው አየር ላይ እንዳይውል መደረጉን ተከትሎ ቢቢሲ በጉዳዩ ላይ የድርጅቱ ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ዝናቡ አስራት እና ምክትላቸውን አቶ ቦጃ ገቢሳ ምላሽ ለማግኘት በስልክ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም የሁለቱም የእጅ ስልክ ባለመነሳቱ ሳይሳካለት መቅረቱን አስነብቧል።

ከዚህም በኋላ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (ኦቢኤን) የቦርድ አባል እና የክልሉ ኮሚኬሽን ቢሮ  ሓላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ “ይህ ሊሆን የሚችልበት ምንም መመዘኛ የለም፤ ይህ ጉዳይ መጣራት አለበት” ሲሉም ዛሬ ተደምጠዋል።

አቶ ጌታቸው ከድርጅቱ እና ከቦርድ አባላት ጋር የዘወትር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውሰው፤ ይህ ጉዳይ ግን በቦርዱ ስብሰባ ላይ እስካሁን አለመነሳቱን ጠቁመው፤ “ሙያው በሚፈቅደው መሠረት አርትኦት ይሠራል እንጂ የዚህ ሰው ድምጽ ይተላለፍ፣ የእዚህ ይከልከል የሚል ሰው የለም” ብለዋል።

LEAVE A REPLY