ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአሜሪካዉ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሬስ ሴክሬታሪ ካንቲ ሚለር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተሰማ:: ይህን ተከትሎም ለጥንቃቄ ሲባል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና ምክትላቸዉ ማይክ ፔንስ በየቀኑ ምርመራ እንዲደረግላቸዉ ተብሏል::
በተጨማሪም ሁለቱ ፕሬዝዳንታቸው ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት የሚገባ የትኛዉም ጉዳይ በልዩ ጥንቃቄ እንዲታይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ከእርሳቸዉ ጋር ተገናኝተዋል የተባሉ ሥድሥት የምክትል ፕሬዝዳንቱ የሥራ አጋሮችም ለጊዜዉም ቢሆን ራሳቸዉን እንዲያገልሉ የተደረገ ሲሆን ፤ ትራምፕና ማይክ ፔንስ ግን ከተጠቂው ካንቲ ሚለር ጋር በቅርቡ ተገናኝተዉ እንደማያዉቁ መረጃዎች እየጠቆሙ ናቸው፡፡
ካንቲ ሚለር የፕሬዝዳንት ትራምፕ ፤ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት ስቴፈን ሚለር ባለቤት ሲሆኑ፣ የእርሳቸዉ በቫይረሱ መጠቃት ቫይረሱ በነጩ ቤተመንግሥት ባሉ ሰዎች በፍጥነት እንዳይዛመት ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ለሥራ አጋሮቻቸዉ ባስተላለፋት መልክዕት፣ መደናገጥ እንደማያስፈልግና የተቻላቸዉን ያህል ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸዉ ተናግረዋል፡፡ በአሜሪካ እስካሁን ከ76 ሺኅ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ለሞት ተዳርገዋል:: አንዳንድ የሀገሪቱ ግዛቶች አሁን ላይየእንቅስቃሴ ገደቡን አንስተዉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴያቸዉ ለመመለስ ዳር ዳር እያሉ ናቸው፡፡