የምዕራብ ዕዝ ሠራዊት የህዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት እየሠራ ነው...

የምዕራብ ዕዝ ሠራዊት የህዳሴው ግድብ ግንባታ ላይ የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት እየሠራ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህዳሴው ግድብ ግንባታ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ የምዕራብ ዕዝ መከላከያ ሠራዊት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ  ነው ተባለ።

የዕዙ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ተመስገን፤ በግድቡ አካባቢ ፀጥታን የማረጋገጥ ሥራዎች በመሥራት ላይ የሚገኙትን የሠራዊት አባላትን በጎበኙበት ወቅት “የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደ ሀገር ትልቅ ትኩረት የተሰጠው፣ ሕዝባችን ፍፃሜውን በከፍተኛ ትኩረት የሚከታተለው ይህን ፕሮጀክት ሠራዊታችንም በንቃት እየጠበቀው ይገኛል”  ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፀጥታ ሥራውን ይበልጥ ለማጠናከር የምዕራብ ዕዝኮማንድ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ሠራዊቱ ዘንድ መነቃቃትና ደስታን ፈጥሯል ብለዋል፡፡

የትኛውም ኃይል የታላቁ ህዳሴ ግድብ የግንባታን ማስቆም አይችልም ያሉት ጀነራሉ፤  ጦሩ በከፍተኛ እልህና ሞራል የተጣለበትን ሓላፊነት ከመወጣት ባሻገር ለሠባተኛ ጊዜ በወር ደመወዙ የቦንድ ግዥ ፈጽሟል ሲሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኩል የህዳሴ ግድብ በመጪው ክረምት ውሃ መሙላት ሂደት እንደሚጀምር ይፋ የተደረገ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የግብፅ መንግስት የአሞላል ሂደቱን ለማጨናገፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዘመቻ በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY