ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ለአደጋ የተጋለጡና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ከ40,000 (ከአርባሺኅ) በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መርሀግብር ይፋ ሆነ፡፡
ይህ መርሃ ግብር “የኔ ቤተሰብ” የሚል መጠሪያ እንደተሰጠውም ሰምተናል፡፡ የእርዳታ መርሀ ግብሩ የተዘጋጀው “ድር ፋውንዴሽን” በተሰኘ የሀገር ውስጥ ግብረ ሰናይ ድርጅት መሆኑም ታውቋል፡፡
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ችግር የገጠማቸውን ከ40 000 በላይ ዜጎች ከለጋሽ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር በማገናኘት ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ የእርዳታ መርሃ ግብሩ ዋነኛ ዓላማ እንደሆነ ዛሬ ተነግሯል፡፡
ድር ፋውንዴሽን በቅርቡ ይፋ ባደረገው ድረ ገፅ አማካኝነት ባሰባሰበው ገንዘብ በአራዳ ክፍለ ከተማ ለሚኖሩ 150 የሚጠጉ አቅመ ደካሞች ለእያንዳዳቸው 2.000 (ሁለት ሺኅ) ብር ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል፡፡